በአዲስ አባባ የተጀመረው የቀን ገቢ ግምት 57 በመቶ ተጠናቀቀ

ግንቦት 10፣ 2009

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የቀን ገቢ ግምት 57 በመቶ መጠናቀቁን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ቀሪው 47 በመቶ የሚሆነውን የቀን የገቢ ግምት እስከ ግንቦት 30 ድረስ እንደሚጠናቀቅም ነው የገለፀው፡፡

አማካኝ የቀን ገቢ ግምት ስራው ከሚያዚያ 17 ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው፡፡

በቀን ገቢ ግመታው ከ2 ሺህ በላይ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የነጋዴዎች ዕቃ ማሸሽ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ታዳጊዎች ሱቅ እንዲጠብቁ ማድረግ እንዲሁም ሌሎች ህገወጥ ተግባራት በገቢ ግመታው እንደችግር የተለዩ ናቸው፡፡

ያለንግድ ፍቃድ የሚጠቀሙ ነጋዴዎችና የዘርፍ ለውጥ ያደረጉ ነጋዴዎችን ለመለየት የአማካኝ የዕለት ገቢ ግምቱ እንደሚጠቅምም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡  

ሪፖርተር፤ አባዲ ወይናይ