በትራምፕ ያልተረጋጋ ፖለቲካ ቱጃሮች 35 ቢሊዮን ዶላር አጡ

ግንቦት 10፣ 2009

የዓለም 5 መቶ ቱጃሮች በትራምፕ ያልተረጋጋ ፖለቲካ በአንድ ቀን ውስጥ 35 ሚሊዮን ዶላር ማጣታቸውን ብሉምበርግ የዜና ወኪል አስነበበ፡፡

ቱጃሮቹ ገቢውን ያጡት ትናንት /ዕሮብ/ በነበረው የአክስዮን ገበያ መቀዛቀዝ በማሳየቱ ነው፡፡

ለዚህ ምክንያት የሆነውም ዶናልድ ትራምፕ ስማቸው ከሩሲያ ጋር መያያዙ እና የፌደራል ምርመራ ቢሮ ሃላፊውን ማሰናበታቸው በአሜሪካ ያለመረጋጋት በመከሰቱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የዓለም ቁጥር አንዱ ቱጃር ቢል ጌትስ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በዕለቱ ማጣቱ ተገልጿል፡፡ የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙገር በርግ ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር በማጣት ከፍተኛ ገቢ ያጣ ቱጃር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች ቱጃሮችም  ከቢሊዮን እስከ ሚሊዮን ዶላሮችን ማጣታቸው ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ፖለቲካ ውዝግብ በቀጣይም  በአሜሪካ አክሲዮን ገበያ መቀዛቀዝ ሊያሳይ እንደሚችል ተዘግቧል፡፡

ምንጭ፤ ብሉምበርግ