ህንድ 10 ተጨማሪ የኒኩሌር ማብላያ ጣቢያዎች ልታቋቁም ነው

ግንቦት 10፣ 2009

የህንድ መንግስት 10 ተጨማሪ ከፍተኛ የኒኩሌር ማብላያ ጣቢያዎች በማቋቋም የአገሪቱን የኒኩሌር አቅም ሊያሳድግ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ህንድ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍጆታ ካላቸው የአለማችን አገራት አንዷ ስትሆን አብዛኛውን ሃይል የምታመነጨው ከድንጋይ ከሰል በሚገኝ ሃይል ነው፡፡ የማብላያ ጣቢያዎቹ አሁን አገሪቱ በኒኩሌር ሀይል ከምታመርተው የኤሌክትሪክ ሃይል በላይ ማምረት የሚያስችላት ሲሆን መቼ ወደ ስራ እንደሚገባ ግን አልተገለጸም፡፡

በህንድ 22 የኒኩሌር ሃይል ማመንጫዎች የሚገኙ ሲሆን 6 ሺህ 780 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ፡፡

አሁን በሚከፈቱት አዳዲስ የማብላያ ጣቢያዎች ከ7 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የህንድ የሃይል ሚንስትሩ ፒዩሰሀ ጎያል ገልጸዋል፡፡

በሚቋቋሙት የኒኩሌር ማብላያ ጣቢያዎች ምክንያት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገበያ የሚፈጥር ሲሆን ከ33 ሺህ በላይ ክፍት የስራ እድልም እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ