የኦሮሚያ ክልልና ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቆሻሻ ክምር አደጋ ለደረሰባቸው ተጎጅዎች የ45 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጡ

መጋቢት 07 ፣2009

የኦሮሚያ ክልል፣ሚድሮክ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ሉ ወንጌል አኞች ቤተክርሰትን  በአዲስ አበባ ቆሻሻ ክምር አደጋ ለደረሰባቸው ተጎጅዎች ማቋቋሚያ የሚውል የ45 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ለተጎጂዎቹ መልሶ ማቋቋሚያ እንዲሆን የለገሰው 5 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

ሚድሮክ ኢትዮጵያና እህት ኩባንያዎቹ  በበኩላቸው የ40 ሚሊዮን ብር ልገሳ ማድረገጋቸውን አስታውቀወዋል፡፡

በማቋቋሙ ሂደት የበኩሉን ለመወጣት መዘጋጀቱንም ሚድሮክ ኢትዮጵያ  አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርሰትያንም ለተጎጂዎች የሚውል የ150 ሺህ ብር ለግሳለች፡፡

ሁሉም ወገኖች  እርዳታውን ዛሬ ነው  የሰጡት ፡፡

የቆሻሻ መደርመስ አደጋው የ113 ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ፣ብዙዎችን ለአካል ጉዳትና ለንብረት ውድመት ዳርጓቸዋል፡፡

የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች እያደረጉት ያለው ድጋፍ በመልሶ ማቋቋሙ ሂደት ጉልህ ሚና እንሚጫውት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገልጿል፡፡

ሪፖርተር ፡‑ ፋሲካ አያሌው