አዲሱ የአሜሪካ የጤና ፖሊሲ 14 ሚሊዮን አሜሪካዊያንን ከጤና መድን ሽፋን ውጭ ሊያደርግ ነው

መጋቢት 05፣2009

የፕሬዝዳንት ትራም የጤና ፖሊሲ 14 ሚሊዮን አሜሪካዊያንን ከጤና መድን ሽፋን ውጭ የሚያደግ እቅድ ይፋ አደረገ፡፡

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ይኸው የትራምፕ የጤና ፖሊሲ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን የጤና ሽፋን ይሰጣቸው የነበሩ አሜሪካዊያንን ቁጥር ዝቅ የሚያደርግ ነው ፡፡

አሁን ይፋ የሆነው የጤና አገልግሎት ፖሊሲ በቀጠቀዩ አመት ወደ ስራ ሲገባ ብዙዎችን የጤና መድን ሽፋን መብት የሚያሳጣ በመሆኑ ትልቅ ቀውስ ይፈጥራል ተብሏል፡፡

እ ኤ አ በ2026 በአገሪቱ የጤና መድን ሽፋን የሌቸው አሜሪካዊያንን ወደ 24 ሚሊዮን ከፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ይሁንጂ አዲስ የቀረበው የጤና መድህን ሽፋን ቅነሳ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ የአገሪቱን የበጀት ጉድለት  በ337 ቢሊዮን ዶላር መቀነስ እንደሚያስችል የአሜሪካ ኮንግረስ አፈጉባኤ ፖል ሪያን ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የጤና መድህን ሽፋን ቅነሳ እቅድ የፕሬዝዳንት  ኦባማ የጤና ፖሊሲን የሚተካ ይሆናል፡፡

ምንጭ ፡‑ ቢቢሲ