ኢትዮጵያና አሜሪካ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የትብብር ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

ህዳር 28፣2010

ኢትዮጵያና አሜሪካ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የትብብር ግንኙነት  ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማማቶ ከተመራ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር በሁለትዮሽ  በአካባቢያዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋር የሆነችው አሜሪካ የምታደርገው ድጋፍ እንዲጠናከር  በሚያስችሉና በተለያዩ  መስኮች የስትራቴጂያዊ አጋርነት ግንኙነታቸውን በሚያጎለብቱ ጭብጦች  ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል..

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና የዴሊቨሪ  ዩኒት ሃላፊ አቶ ዛድግ አብረሃ ውይይቱ በ3 አብይ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደርና የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሩ ዶናልድ ያማማቶም ኢትዮጵያ የሀገራቸው ዋንኛ አጋር እንደሆነች ገልጸዋል፡፡