በሠመራ የተገነባው አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመርቆ ለስራ ክፍት ሆነ

ህዳር 28፣2010

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠመራ ከተማ የተገነባው አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመርቆ ለስራ ክፍት ሆነ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ ስዩም አወል የተመረቀው አየር ማረፊያው ከ45ዐ ሚሊየን ብር በላይ መፍጀቱ ታውቋል፡፡

የአፋር ክልል ካለው የማዕድን ሃብት የአዋሽ ወንዝን ተከትሎ ካለው ኢንቨስትመንት እንዲሁም ከጅቡቲና ከታጁራ ወደብ ካለው ግንኙነት አንፃር አየር ማረፊያው ለክልሉም ሆነ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ዕድገት አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን በምረቃው ወቅት ተጠቅሷል፡፡

ሪፖርተር፡‑ በላይ ሀድጉ