እየሩሳሌም የእስራኤል መዲና እንድትሆን አሜሪካ እውቅና መስጠቷ እንዳሳሰበው የአፍሪካ ህብረት ገለፀ

ህዳር 28፣2010

አሜሪካ የእስራኤል ዋና ከተማ እየሩሳሌም እንድትሆን ዕውቅና መስጠቷ እንዳሳሰበው የአፍሪካ ህብረት ገለጸ፡፡

የአሜሪካ ውሳኔ የአካባቢውን ውጥረት እንደሚያባብስና ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚያሰናክለው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ለቀመንበር ሙሳ ፋኪህ ተናግረዋል፡፡

ፍልስጤም ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ በማድረግ ሉኣላዊ ሀገር ለመሆን የሚታደርገውን ጥረት ህብረቱ አንደሚደግፍም ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረትና የመንግስታቱ ድርጅት የሚከተለውን ደህንነታቸው የተረጋገጠ እስራኤልና ፍልስጤም ጎን ለጎን የሚመሰረቱበት አለም አቀፍ ጥረት ዳግም እንዲጀምር ህብረቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፣ አፍሪካ ህብረት