ኢትዮጵያና ጅቡቲ በቱሪዝም ዘርፍ በጋራ ለመስራት የንግድ ለንግድ ውይይት አካሂደዋል

ህዳር 28፣2010

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በቱሪዝም ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የንግድ ለንግድ ውይይት በጅቡቲ አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አስጎብኚዎች ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱ በተለያዩ ጊዜያቶች የሚመጡ ጎብኚዎች በሁለቱም ሀገራት ቆይታ እንዲኖራቸው በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

ይህም የሀገራቱ ዜጎች ከሚያደርጉት የተናጥል ጉብኝት በተጨማሪ የሌሎች ሀገር ዜጎችን በሁለቱም ሀገራት ጉብኝት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ካላቸው የቱሪዝም ሀብት አንፃር መድረኩ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር የቻለ ምህረት ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቱሪዝም ዘርፍ በውድድር ሳይሆን ክፍተታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙበት ይሆናልም ብለዋል፡፡          

ሪፖርተር፡‑ ሁናቸው ታዬ