በኢትዮጵያ አሁን ባለው የህዝብ ዕድገት ወጥ አምራች የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ

ህዳር 28፣2010

በኢትዮጵያ አሁን ባለው የህዝብ ዕድገት ወጥ አምራች የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ  አካዳሚ ባዘጋጀው 3ኛው የሳይንስ ኮንግረስ ላይ እንደተጠቀሰው በሀገሪቱ አሁን ባለው የስነ ህዝብ አወቃቀር መሰረት ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ እድሜው ከ24 አመት በታችና በአመዛኙ  አምራች አይደለም ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፅጌ ገብረማርያም የሀገሪቱን የአምራች ህብረተሰብ ቁጥር ለመጨመር የዜጎችየወሊድ ምጣኔ ዝቅተኛ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ወደስራ ለማስገባትም የሀገሪቱን የስነ-ህዝብ አወቃቀር መሠረት ያደረገ የዕድገት ዕቅድ እንደሚያስፈልግም  ፕሮፌሰር ፅጌ   ተናግረዋል፡፡