ብሄሮች ብሄረሰቦች በአንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ግንባታ ላይ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡‑ ጠ/ሚ ኃይለማርያም

ህዳር 28፣2010

የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት በተጀመረው የኢትዮጵያ ህዳሴ የጋራ ፕሮጀክት ስኬታማ ተግባር ማከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ሀገር እንዲኖራቸው አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በመገንባት ሂደት ውጤታማ መሆኑ ባለፉት 25 ዓመታትና ከዚያ ወዲህ የተሰሩ ስራዎች ህያው ምስክር ናቸው ብለዋል፡፡

በፖለቲካም ሆነ በኢኮኖሚው ዘርፎች  የተመዘገቡ ለውጦች ለሀገሪŸ ህዳሴ የተሄደው ረጅም ርቀት ስኬታማ መሆኑን እንደሚያመለክትም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገልፀዋል፡፡

ከድህነት ለመዉጣትና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የተገኘውን ሀብት ለመቀራመት የሚፈልግ ሀይል በመኖሩ ለህዳሴ ጉዞው መሰረታዊ ተግዳሮት መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ህዝቡ ከእነዚህ ሀይሎች ጋር የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡