ኡጋንዳ በሶማሊያ የአሚሶም አካል የነበረውን የሰላም አስከባሪ ጦሯን ማስወጣት ጀመረች

ህዳር 28፣2010

ኡጋንዳ በሶማሊያ የአሚሶም አካል የነበረውን የሰላም አስከባሪ ጦሯን ማስወጣት ጀመረች፡፡

የኡጋንዳ መከላከያ ኃይል እዳስታወቀው በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሉ ስር ተሰማርቶ ከነበረው ጦሩ ከፊሉን ማስወጣት ጀምሯል፡፡

የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት ስር ከተሰማራው ኃይል 1ሺህ ወታደሮች  እስከተያዘው ወር መጨረሻ እንዲቀነሱ ባስቀመጠው አቅጣጫ  ኡጋንዳ 281 ያህል ወታደሮቿን እንደምታስወጣ ገልፃለች፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሂደት ስር 20 ሺህ ወታደሮች ይገኛሉ፡፡ከዚህ ውስጥ ትልቁን መዋጮ በ6ሺህ ጦር  የያዘችው ኡጋንዳ መሆኗን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

እንደዘገባው የሰላም አስከባሪ ካዋጡ አገራት መካል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብሩንዲ ፣ ኬንያና ጅቡቲም ወታደሮቻቸውን ከሚቀንሱ አገራት መካከል ይገኙበታል፡፡

ሶማሊያ በገጠማት አለመረጋጋትና አልሸባብ እያደረሰ ካለው የፀጥታ ስጋት ለመታደግና ለአገሪቱ ጦር እርዳታ ለማድረግ በተባበሩት መንግስታትና በአፍሪካ ህብረት ውሳኔ ነበር እ.ኤ.አ በ2007 ተመስርቶ  ወደ ስፍራው ያቀናው ፡፡