ሊቢያ ለምታካሂደው ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ማካሄድ ጀመረች

ህዳር 28፣2010

ሊቢያ ለምታካሂደው ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ማካሄድ ጀመረች፡፡

የሊቢያ የምርጫ ባስልጣናት ትላንት እንዳስታወቁት የምርጫው ጊዜ ተቆርጦ ባይወሰንም  የመራጨች ምዝገባው ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ይቆያል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ሊቢያዊያንም በኢንተርኔት በቀጥታ ምርጫ ምዝገባው እንደሚካተቱ በተመድ የሊቢያ መልዕክተኛ ገሳን ሰላም ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሁለት ተከፍሎ ያለውን የሊቢያ መንግስት እርቅ አውርዶ በአዲስ ምርጫ ፖለቲካዊ ሽግግር እንዲመጣ በመስራት ላይ መሆኑም ይታወቃል፡፡

በሊቢያ እ.ኤ.አ በ2011 በጀመረው ህዝባዊ አመፅ  የቀድሞ መሪ  ሙዓመር ጋዳፊ ከስልጣን ላይ ተወግደው ከተገደሉ በኃላ፣ እስካአሁን በማያባራ ግጭት ውስጥ ትገኛለች፡፡

ሊቢያም እስካአሁን ወጥ በሆነ መልኩ የሚመራት መንግስት የሌላት አገር ሆና በሽፍቶች መፈንጫነቷ ትታወቃች ፡፡

በቅርቡም መንግስት አልባ በሆነችው በዚህችው ሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች በባርነት ሲሸጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መውጣቱ ብዙዎችን ማስቆጣቱም የሚታወቅ ነው፡፡

 ምንጭ፡‑ ሲጂቲኤን