ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እዉቅና ሰጡ

ህዳር 27፣2010

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እዉቅና ሰጡ፡፡

የእስራኤልና የፍልስጤም የግጭት መነሻ ከሆኑት የይገባኛል ይዞታዎች መካከል አንዷ ለሆነችዉ እየሩሳሌም በአሜሪካ እዉቅና መሰጠቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለዉን ግጭት እንዳያባብሰው ወደከፋ ቀዉስ ተሰግቷል፡፡

የፍልስጤም ባለስልጣናትም አሜሪካ በእየሩሳሌም ላይ ያላትን ፖሊሲ መቀየሯ በፍልስጤም ላይ ብቻ ሳይሆን በመካከለኛዉ ምስራቅ ላይ ጦርነት እንደማወጅ ነዉ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ ከቴልአቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማዘዋወር ዝግጅት እንዲያደርግ  ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማዘዛቸው ተነግሯል፡፡

እስራኤል እንደሀገር ከተመሰረተች ከአውሮፓውያኑ 1948 ጀምሮ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጋ እዉቅና ስትሰጥ አሜሪካ የመጀመሪያዋ አገር መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡