የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

ህዳር 27፣2010

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በአዲስ አበባ በህዳር ወር ሲሸጥ ከነበረበት የ45  ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበት በ21 ብር ከ 06 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ የመውጣት እና የመውረድ ሁኔታ ቢታይም በሀገሪቱ በቅርቡ የተደረገው  የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ ጋር ተዳምሮ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ተፅእኖ እንዳያሳድር የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ በላከልን መግለጫ አስታውቋል፡፡