የአየር ብክለት የህጻናት አእምሮ እየጎዳ ነው:- ዩኒሴፍ

ህዳር 27፣2010

17ሚሊዮን የሚሆኑ ከአንድ አመት በታች ያሉ ህጻናት በመርዛማ አየር ምክንያት የአእምሮ እድገታቸው ለአደጋ የተጋለጠ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ አስጠነቀቀ።

በደቡብ ኤስያ አገራት በተበከለ አየር አከባቢ የሚኖሩ 12ሚሊዮን ህጻናት በደህና አከባቢ ከሚኖሩ በስድስት እጥፍ ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውንም አመልክቷል።

በምስራቅ ኤስያና ፓስፊክ አገራት የሚኖሩ አራት ሚሊዮን ህጻናትም አደጋ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

ዩኒሴፍ እንደገለጸው የአየር ብክለት የአንጎል ህዋሳትን ይጎዳል የአእምሮ እድገትንም ሊያዳክም ይችላል። ከዛም አልፎ ሞት ሊያስከትል እንደሚችል መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።