አፍሪካ የአከባቢ አያያዝ ስራን ከቻይና ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለጸች

ህዳር 27፣2010

የአፍሪካ የአከባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች የአህጉሪቱን የደን  መጨፍጨፍ እና የአየር ብክለትን ለመከላከል   የቻይና የአከባቢ  አያያዝ  ልምድ  መቅሰም  እንደሚፈልጉ  አስታወቁ፡፡

የአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ፓኮሜ ሞዩቤሌት ቦዩቤያ አህጉሪቱን ከብክለት ከአከባቢ ችግር ለመታደግ   በደን አያያዝ   እና ከአየር ብክለት ለመከላከል  ከቻይና ትልቅ ልምድ ለመቅሰም እቅድ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የጋቦን የደን፣የባህር እና የአከባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እና በአከባቢ ጥበቃ ጉባኤ የአፍሪካ ሚንስትሮች ፕሬዝዳንት ፓኮሜ ሞዩቤሌት ቦዩቤያ ከብክለት የፀዳች አለም በሚል መሪ ቃል በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ የአከባቢ ሚንስትሮች ጉባኤ ላይ  አህጉሪቱ  የአፍሪካ ህብረት የ2063  አጀንዳና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት  የደቡብ -ደቡብ ትብብርን በአጽንኦት ትተገብራለች ብለዋል፡፡  

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመጣው የቻይና አፍሪካ ዘርፈ ብዙ ትብብር   አፍሪካ  የቻይናን   ጥንካሬ እና  ሀገር በቀል  እውቀቶቿን መቅሰም  እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡  

  ሚንስትሩ እንዳሉት አፍሪካ ችግሮቿን ለመቅረፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ትወስዳለች እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማላመዷን ታሳድጋለች።  

ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ የአከባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአከባቢያዊ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ የሚያወጣቸውን ውሳኔዎችን ለማጽደቅ ዝግጁ መሆናቸው መግለጻቸውን ሽንዋ  ዘግቧል።