በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ የአገራቸው መመለሳቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ

ህዳር 27፣2010

በመቶዎች የሚቆጠሩ በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ወደ የሃገራቸው መመለሳቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ ፡፡

ፈቃደኛ ስደተኞችን ለመመለስ አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከሊቢያ መንግስት ጋር በሰራው ስራ 403 ስደተኞችን ወደ መጡበት መመለሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ህገ ወጥ ስደተኞችን በመመለስ ሂደት ውስጥ 150 ናይጄሪያ ዜጎች ተመልስዋል፡፡

200 የሚሆኑ ከተለያዩ አገራት የመጡ ህገ ወጥ ስደተኞችን ባለፈው የፈረንጆች ጥቅምት ወር ላይ መመለሳቸውን የሚስራታ እስር ቤት አዛዥ አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይ ቀናትም ሌሎች 60 ስደተኞችን ወደየአገራቸው ለመመለስ በዕቅድ መያዛቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት  ያለረዳት የቀሩ ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደሃገራቸው ለመመለስ በሚደረግ ጥረት ውስጥ የትሪፖሊ አየር መንገድ 253 የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ናይጄሪያ መመለሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡