በአፍሪካ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለዉጥ ለማምጣት የመብራት ሀይል ችግሮች እንዲፈቱ ተጠየቀ

ህዳር 27፣2010

በአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለዉጥ ለማምጣት የመብራት ሀይል ችግሮች እንዲፈቱ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለዉ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ጉባኤ የአምራች ኢንዱስትሪዉን ለማሳደግ የመብራት ሀይል አቅርቦቱ መሻሻል አለበት ተብሏል፡፡

የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዉ እንዲደርሱም የግሉ ዘርፍ መበረታታት እንዳለበት ተነስቷል፡፡

ለዚህም የመንግስታዊ ተቋማት አቅም እና አስተዳደር ፈጣን እድገት ሊያሳዩ ይገባቸዋል ብሏል ጉባኤዉ፡፡