ኢንጂነር አዜብ አስናቀ የአመቱ ምርጥ ሴት ተብለው ተሰየሙ

ህዳር 27፣2010

አለም አቀፉ ፓወር ጄኔሬሽን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በኢትዮጵያ  የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል ለሰሩት ከፍተኛ ሥራ የ2017 ምርጥ ሴት ብሎ ሰየማቸው።

ኢንጂነር አዜንብ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታ፣ በሀይል ማመንጫ የማስተላለፊያ መስመሮች እንዲሁም ለጎረቤት ሱዳን፣ ጂቡቲና ለኬንያ የድንበር ከተሞች የኤሌክትሪክ ሽያጭ ቁጥጥር የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው በአግባቡ መወጣቸው  ለመመረጣቸው እንደ አብነት ጠቅሷል።

ኢንጂኔር አዜብ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኢንዱስትሪ ሲቀላቀሉ ኢትዮጵያ ከውሀ  2,430 ሜጋ ዋት ታመነጭ እንደነበረ ያመለከተው ዘገባው በእርሳቸው መሪነት  4,500 ሜጋ ዋት ደርሷል ብሏል᎓᎓

በእርሳቸው የአመራር ዘመን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል በአውሮፓውያኑ 2020 17ሺህ ሜጋ ዋት በማመንጨት የአፍሪካ የሀይል ማእከል በማድረግ አገሪቱን ወደ መካከለኛ ኢኮኖሚ እንዲሸጋገር የሚያስችል ስርዓት መፍጠር  እንደሆነም ተገልጿል᎓᎓

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ የኢትዮጵያ ዋና የኢኮኖሚ ዘርፍ የሆነውን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ ሴቶችን በምህንድስና ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ታላቅ ስኬት ሊያመጡ እንደሚችሉ ማሳያ ናቸው ሲል የዘገበው ፓወር ኢንጂኔሪንግ ነው᎓᎓