ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ አዋጁ ላይ ያካሄዱት ድርድር ውጤታማ እንደነበር ገለፁ

ህዳር 26፣2010

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ምርጫ አዋጅ ላይ ያካሄዱት ድርድር ውጤታማ እንደነበር የአስራ አንዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ አስታወቀ፡፡

ይህን አስመልክቶም ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ስብስብ ከኢህአዲግ ጋር ባደረጉት ድርድር የምርጫ ስርዓቱን ከመቀየር  ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 የተለያዩ አንቀፆች ላይ ማሻሻያ እንዲካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

የጀመሩትን ድርድር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት የአስራ አንዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ከምርጫ ቦርድ አደረጃጀትና ስያሜ ጋር በተገናኘ በድርድሩ የተነሱ ሀሳቦች በመገናኛ ብዙሀን በአግባቡ አልቀረቡም ብለዋል፡፡