በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህዝቦች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናከር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ

ህዳር 26፣2010

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህዝቦች መካከል ያለውን የህዝብ  ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርና ሁለቱ ክልሎች በጋራ የሚሰሩዋቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች ለማጎልበት የሚረዳ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ ፡፡

በምክክር መደረኩ በክልሎቹ ያለውን በመተባበር ላይ መሰረት ያደረገ የአብሮ መኖር እሴትን ማሳደግ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን በክልሎቹ ተግባራዊ የሚደረግ የሁለትዮሽ የሰላም እና የልማት ዕቅድም ፀድቋል ፡፡

የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው የብሄር ብሄረሰብ ስብጥር እና አኗኗር ምሳሌ እንደሚሆን የገለጹ ሲሆን የህዝቦችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል እና ድህነትን መቀነስ ላይም ሁለቱ ክልሎች በአንድነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው የሁለቱን ክልል ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው ክልሎቹን በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማስተሳሰር ዕቅዶች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል ፡፡

ሪፖርተር፡‑  ተመስገን ሽፈራው