ህገ መንግስቱን ሁሉም ህብረተሰብ እንዲያውቀው ለማስቻል ከትምህርት ቤት ጀምሮ በስፋት እንዲሰራ ተጠየቀ

ህዳር 26፣2010

ህገ መንግስቱን ሁሉም ህብረተሰብ እንዲያውቀው ለማስቻል ከትምህርት ቤት ጀምሮ  በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በሰመራ የ12ኛው ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በአልን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል በህገ-መንግስቱ ዙሪያ ያተኮረ የጥያቄ እና መልስ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በአፋር ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአብዴፓ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አምባሣደር ሀሰን አብዱልቃድር በሰመራ የሚከበረው በአል በህገ መንግስቱ በተገኙ ድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ የበአሉ ተሳታፊዎች ግንዛቤ የሚፈጥሩበት ነው ብለዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ-መንግስት አስተምህሮ እና ሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሪት ፍረወይኒ ገ/እግዚአብሔር በበኩላቸው ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱ በማህበረሰቡ አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርፅ ለማስቻል አስተምህሮው ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የትምህርት ተቋማት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

በተማሪዎች መካከል የተካሄደው የጥያቄ እና መልስ ውድድርም በህገ መንግስቱ እና ፌደራሊዝም ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

 ሪፖርተር ፡‑ አስማማው አየነው