የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገራት እንዲያገለግሉ 4 ቆንስል ጄኔራሎችን ሾሟል

ህዳር 26፣2010

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ የኢስያ አገራት የሚያገለግሉ ለአራት ቆንስል ጄኔራሎች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት  ለአራት ግለሰቦች  በባለ ሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ማዕረግ ቆንስል ጄኔራል ሆነው በተያዩ የኢስያ አገራት ከተሞች እንዲያገለግሉ ሚኒስቴሩ የስራ ምደባ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

1.አምባሳደር ዋህደ በላይ በሊባኖስ የቤይሩት 

2.አቶ ደመቀ አጥናፉ  በህንድ ሙምባይ

3.አቶ ተፈሪ መለስ  በቻይና ጓንጁ እና

4.ወይዘሮ እየሩሳሌም አምደማሪያም በተባበሩት አረብ ኢምሬት የዱባይ የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል᎓᎓

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ በዋናው መስሪያ ቤት በተለያዩ ዘርፎችም ዳይሬክተር ጀነራል ሆነው እንዲያገለግሉ ለ13 ተሻሚዎች ምደባ መስጠቱን አስታውቋል፡፡