የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል

26 ፣2010

የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶናልድ  ያማሞቶ  የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝታቸውን በሶማሊያ ጀምረዋል፡፡

ዶናልድ  ያማሞቶ   በሶማሊያን  በኬንያ፣ ኢትዮጵያን  እና ሩዋንዳን የሚያካሂዱትን ጉብኝት ትላንት በሶማሊያ የሰላም ጉዳይ ጀምረዋል፡፡ 

ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የሶማሊያ የደህንነት ተቋማትንና ማጠናከርና መረጋጋት ላይ አትኩሮ በፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ በተመራው ስብሰባ ተካፍለዋል᎓᎓ 

ከሶማሊያ መልስ ዶናልድ ያማማቶ ወደ ናይሮቢ ኬንያ ተጉዘው  ከኬንያ መንግሥት ተወካዮች እና  የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ጋር ይገናኛሉ ተብሏል᎓᎓በጉብኝታቸው  በኬንያ  ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይት አለዝበው ሰላም በሚወርድበት ሁኔታ ላይ የሚመክሩ ይሆናል፡፡ 

በአዲስ አበባ በመገኘትም  ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት አመራሮች ጋር   ውይይት እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል᎓᎓ በሁለቱ ሀገራት መካከል በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ውይይቶችን ከማድረጋቸው  በተጨማሪ  ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣኖች  ጋር የምግብ ዋስትናን፤ የሰላም አስከባሪን እና የስደተኞች ጉዳዮችን ጨምሮ ስለ ክልላዊ ጉዳዮች  እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድረ ገፁ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል᎓᎓

ተጠባባቂ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሌላው የቀጠናው ጉብኝታቸው  ወደ ኪጋሊ ሩዋንዳ በመጓዝ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዝዳንትነትን በቅርቡ ከሚረከቡት ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአፍሪካ  ጉዳዮች የአሜሪካ ተጠባባቂ ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው በምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት  ዶናልድ ያማማቶ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መምህር ከመሆናውም ባሻገር፣ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ድፕሎማት ናቸው፡፡