በሰመራ ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል እንግዶች አፋር መግባት ጀምረዋል

26 ፣2010

ለ12ኛ ጊዜ በአፋር ክልል ሰመራ ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ከተለያዩ ክልል የመጡ የባህል ቡድኖች አፋር አሚባራ ወረዳ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡

ታዳሚዎቹ በተደረገላቸው አቀባበል እንደተደሰቱና የክልሉ ህዝብ ያለውን እንግዳ ተቀባይነት ያዩበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሩን ያደረጉት የአሚባራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰኢሌ ሃሺም የሰው ዘር መገኛ የሆነው የአፋር ህዝብ በፌደራሊዝም ስርአት ትሩፋት ተጠቃሚ ከሆኑት ብሄሮች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የፌደራሊዝም ስርአቱን የተሳሳተ እንደሆነ በማስመሰል ህዝብን ለማሳሳት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን አጥበቆ መታገል እንደሚገባና የኢትዮጵያ ብሄሮች ቀድመን የምንታወቅበትን አንድነት አጠናክረን ልንቀጥል ይገባልም ብለዋል፡፡

በአሉን ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን የመቀበልና ወደርእሰ ከተማዋ ሰመራ የመሸኘቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡