የፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማት በተሰማሩበት የስራ መስክ ወጥ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተጠይቋል

26 ፣2010

ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማት በተሰማሩበት የስራ መስክ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ቢኖራቸው ለተልዕኳቸው መሳካት የተሻለ አቅም እንደሚፈጥር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስትሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለፁ፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱና የሁሉም ክልሎችና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር ፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማት የሩብ ዓመት የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂደዋል፡፡

ፍላጎቱ እያደገ የመጣውን የአገልግሎት አሰጣጥ ወቅቱ በሚጠይቀው ደረጃ ላይ ለማስቀመጥ አልሞ ለተቋማቱ ሰራተኞች የተሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰረት በማድረግ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የተቋማቱ ፍፃሜዎች ወጥ የሆነ ስራ መሰራት እንደሚገባም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

በጥቂት ዓመታት ውስጥ ዘርፉን ለማዘመንና የተቀናጀ የመረጃ ስርዓትን በሁሉም ተቋማት ለመዘርጋት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካትም ይሰራል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የየክልሉና ከተማ መስተዳድር የፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማቱ የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት አካሂደዋል፡፡

የሪፖርተር፡‑ ዳዊት ጣሰው