አካል ጉዳተኞችን ተደራሽና ተጠቃሚ ለማድረግ የወጡ ፖሊሲዎችና ህጎች ተግባራዊ እየተደረጉ አይደለም ተባለ

 26 ፣2010

አካል ጉዳተኞችን ተደራሽና ተጠቃሚ ለማድረግ የወጡ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ አይደለም ተባለ፡፡

26ተኛው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበሯል፡፡

አካል ጉዳተኞችን ተደራሽና ተጠቃሚ ለማድረግ  አገሪቱ ያወጣቻቸው የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ ባለመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን አስገንዝቧል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ወ/ት ቃልኪዳን ሽመልስ በፌዴሬሽኑ በኩል የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተያዘው ዓመት የካቲት ወር ላይ በሚካሄደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መላው ህብረተሰብ አካል ጉዳተኛ እንዲቆጠሩ የማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ታደለች ዳሌቾ የአካል ጉዳተኞችን ችግር ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሪፖርተር፡‑  ብሩክ ተስፋዬ