የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የጣሉት የጉዞ እገዳ እንዲተገበር አፀደቀ

ህዳር 26 ፣2010

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  የስምንት አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለሶስተኛ ጊዜ ያወጡት ህግ እንዲተገበር የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፈቅዷል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትላንት ሰኞ በዋለው ችሎት  በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሻሎ የቀረበውን  የጉዞ እገዳ እንዳይፀና በስር ፍርድ ቤቶች  የተላለፈውን ውሳኔ  በመሻር ህጉ  ተግባር ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም ውሳኔው  የሶሪያ፣ የኢራን፣ ቻድ፣ የመን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያና የሰሜን ኮሪያ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ መግባት እንዳይችሉ የሚያደርግ ሲሆን፣ የቬንዙዌላ ጥቂት ሹማምነቶችንም እገዳው ይነካቸዋል፡፡

በፕሬዝዳንት ትራምፕ የተረቀቀው 3ኛው  የጎዞ እገዳ ባለፈው መስከረም ነበር ይፋ የተደረገው፡፡

ውሳኔው የአሜሪካን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚበጅ ነው ብሎ የፕሬዝዳንት ትራም አስተዳደር ቢከራከርም፣ ተችዎች ግን እገዳው ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ መድልኦ ነው በሚል ሲያጣጥሉት ይሰማል፡፡  

ምንጭ፡‑ ሽንዋ