የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል በሱዳን ሲያካሂድ የነበረውን ወታደራዊ ልምምድ አጠናቀቀ

ህዳር 25-2010

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል  በምስራቃዊ   ሱዳን  በጌቴይት ወታደራዊ ማዘዣ ጣብያ  ሲያሂድ የነበረውን ወታደራዊ ልምምድ አጠናቋል፡፡

ተጠባባቂ ኃይሉ ከሱዳን፣ ከሶማሊያ፤ ከጂቡቲ፣ ከኬኒያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከሲሼልሽ፣ ከኮሞሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከሩዋንዳ እና ከቡሩንዲ  የተውጣጣ  ነው፡፡

የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር  አዋድ ኢብን  አዩፍ  በልምምድ ስነ ስርአቱ ላይ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ልምምድ  በአንዳንድ  የቀጠነው  ሀገሮች የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችን ለመዋጋት ዝግጁነቱን ለመረጋገጥ  ነው ብለዋል፡፡

በአንዳንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች አሁንም የእርስ በርስ  ግጭቶች እና የአሸባሪዎች  እንቅስቃሴ  መኖራቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም ጊዜው  አሁን ነው ብለዋል፡፡

የተጠባባቂ ኃይሉ  ተልእኮ ዋና ሀላፊ አምባሳደር  እስማኢል ቻንፊ  ወታደራዊ ልምምዱ የቀጠናውን የሰላም ተልእኮ ለመወጣት  ባለስልጣኑ  ወታደሮችን የመላክ ኃላፊነት እንዳለውና  ለዚህም  በዘርፉ የሰለጠነ ሰራዊት ሊኖረው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የቀጠናው ተጠባባቂ ኃይል ከፍ ባለ ሙያዊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በልምምዱ መስተዋሉን ተናግረዋል፡፡    

ምንጭ ፡- ሲጂቲኤን