የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ አውደ ርእይ በናይሮቢ እየተካሄደ ነው

ህዳር 25፣2010

የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ አውደ ርእይ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ይገኛል።

በቻይና እና በተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ መርሀ ግብር የሚደገፈው አውደ ርእዩ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የተሰሩ ከመላው አለም የተውጣጡ ከ40 በላይ የፈጠራ ስራዎች እየቀረቡበት ነው፡፡

የአውሮፓውያኑ 2017 የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አውደ ርእይ ቀጣይነት ያለው የአካባቢ ጥበቃ ለአረንጓዴ ልማት በሚል መርህ ነው እየተከበረ ያለው፡፡

በአውደ ርእዩ የፈጠራ ስራቸውን እያቀረቡ ካሉት ተሳታፊዎች መካከል የተሻለ መፍትሄ ይዞ የመጣ ተመርጦ  በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተሸላሚ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

የአውደ ርእዩ መዘጋጀት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲያስመዘግብ ቻይና ያለባትን ሀላፊነት ለመወጣት ያግዛል  ያሉት  በተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የቻይና ተወካይ ሳን ዛይድ ሺጋኝ የቻይና ኩባንያዎችም በአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ተሳትፎ ያሳድጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ውጭም ቻይና ከአፍሪካና ከታዳጊ ሀገራት ጋር ያደረገችውን ስምምነት ለመጠበቅና  በአውሮፓውያኑ 2030 በተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የተቀመጠውን  ግብ ለማሳካትም አውደርእዩ  ያግዛል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡