የሀገር አቀፍ ተዳራዳሪ ፓርቲዎች ድርድር የፖለቲካ ምህዳሩን ያጎለብታል ተባለ

ህዳር 24፤2010

የሀገር አቀፍ ተዳራዳሪ ፓርቲዎች እስካሁን ያደረጉት ድርድር የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲንና የፖለቲካ ምህዳሩን በማጎልበት የራሱ እተዋፅኦ ማበርከቱ ተገለፀ፡፡

የፓርቲዎቹ የድርድር ሂደትና አጠቃላይ አፈፃፀም አስመለልክቶ ግምገማዊ መድረክ ተካሂዷል፡፡

እስካሁን በተካሄደው ድርድር ከአስራ ሁለት የመደራደርያ አጀንዳዎች 3ቱን ተጠናቀዋል፡፡ በመድረኩም በሶስቱ አጀንደዎች  ላይ ግምገማ ተደርጓል፡፡

የጊዜ አጠቃቀም፣ የአሰራር ደንብ አከባበር፣ የስነምግባር ጉዳይ የታዛቢዎች ሁኔታና የሚዲያ አጠቃቀም ውይይት የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡

የድርድሩ ታዛቢዎች ድርድሩ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጎልበት አስተዋፅ እንዳበረከተ ገልፀው የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡