በአፍሪካ መድሃኒቶችን የሚቋቋሙ የወባ ትንኞች እየተስፋፉ ነው ተባለ

ህዳር 22፣2010

በአፍሪካ የትንኝ ማጥፊያ መድሃኒቶችን የሚቋቋሙ የወባ ትንኞች እየተበራከቱ መሆኑን በእንግሊዝ የተደረገ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

እንደጥናቱ ከሆነ ትንኞቹ ለተባይ መግደያ ታስበው የተዘረጉ አንጎበሮችን እና የሚረጩ የትንኝ መግደያ መርዞችን መቋቋም አሳይተዋል፡፡ ይህም የወባ ትንኝን ስርጭት ለመከላከል የተያዘውን መንገድ አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል፡፡

መድሃኒቶችን ለመላመድ ያስቻላቸው የዘረመል ባህሪያቸው መለያየት እና በወባ ትንኝ ፍልሰት  ምክንያት እንደሆነ ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ይህም ለዘርፉ ተመራማሪዎች አዲስ ጥያቄ አስነስቷል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውጤታማ መድሃኒቶች እና ፀረ ትንኝ ቅመሞችን ሊያዘጋጅ እንደሚገባ ጥናቱ መክሯል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳመላከተው ባለፈው ዓመት 216 ሚሊዮን ህዝብ በወባ በሽታ የተጠቃ ሲሆን 445ሺህ የሚሆኑት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ህፃናት እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ