የአፍሪካ ሚንስትሮች የበለፀገ የአይሲቲና ኮሙኒኬሽን ልማት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ

ህዳር 18፣2019

የአፍሪካን የኮሚኒኬሽን፣ አይ ሲቲና የፖስታን አገልግሎት ማዘመን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የአህጉሪቱ የዘርፉ ሚንስትሮች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የተካፈሉ የዘርፉ ሚንስትሮች በአፍሪካ የኮሚኒኬሽንና አይ ሲቲ ዘርፍ ላይ ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉ አህጉራዊና ቀጠናዊ መርሃ ግብሮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል፡፡

በዘርፉ በርካታ ስኬቶች ቢመዘገቡም በአፍሪካ የኮሚኒኬሽንና አይ ሲቲ ዘርፍ በርካታ ችግሮች ተጋርጠውበታል ተብሏል፡፡

የአፍሪካን የአይሲቲና ኮሙኒኬሽን በስፋት ጥቅም ላይ ማዋል ጠቃሚና በአህጉሪቱ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እድል የሚፈጥር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

በአፍሪካ የኮሙንኬሽና አይሲቲ መርሃ ግብርን መዘርጋት የ2063 የአፍሪካን የልማት አጀንዳን እንዲሁም፣ የ2030 የተባበሩት መንግስታትን የልማት ግብን ለማሳካት ምቹ መደላደል የሚፈጥር እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በኮምፒውተር ደህንነት ስትራቴጂ ላይ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንና ፖሊሲ አርቃቂዎች ምክር የሚሰጥ የአፍሪካ የኮምፒውተር ደህንነት ትብብርና ቅንጅት ኮሚቴ ሊቋቋም እንደሚገባ በጉባኤው ምክረ አሳብ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ኒውስ ጋና