ሲንጋፖር አሽከርካሪ አልባ አውቶብሶችን መጠቀም ልትጀምር ነው

ህዳር 14፡2010

ሲንጋፖር በቀጣይ 5 አመታት ጊዜ ውስጥ ሹፌር አልባ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ስራ ለማስጀመር ማቀዷን አስታውቃለች፡፡

የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸውና ለአውቶብሶቹ ምቹ የሆኑ መንገዶች አሉባቸው በተባሉት 3 መንደሮች ነው አገልግሎቱ ይጀመራል የተባለው፡፡

አውቶብሶቹ የአካባቢውን ነዋሪዎች ወደ አቅራቢያ ስፍራዎችና ወደ ባቡር ጣቢያ ያመላልሳሉም ተብሏል፡፡

የአሽከርካሪ  አልባ አውቶቢሶች  አገልግሎት ሲጀመር በተለይ ለአቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና ህፃናት የተሻለ የትራንስፖት አማራጭ እንደሚፈጥር የአገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የአሽከርካሪ አልባ ቴክኖሎጂ አገሪቱ ያላት መሬት በአግባቡ ለመጠቀምና  የሰው ኃይል እጥረትን ለመቅረፍ ይረዳታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሲነጋፖር ከሌሎች የደቡብ ምስራቅ እስያ  ከተሞች ስትነፃፀር የትራፊክ ጭንቅንቅ የሌለባትና የተሻሉ ዘመናዊ መንገዶች እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርትን የሚያበረታታ ፖሊሲ ያላት አገር ነች፡፡

በሲንጋፖር 10 የአሽከርካሪ አልባ መኪና አምራች ኩባንያዎች መኪኖቻቸውን እየሞከሩ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ