የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር የተያዘለትን ዓላማ ማሳካት በሚያስችል መልኩ እየተካሄደ ነው:-ኢህአዴግ

ህዳር 13 ፣2010

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እያካሄዱት የሚገኘው ድርድር የተያዘለትን ዓላማ ማሳካት በሚያስችል መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ ኢህአዴግ አስታወቀ።

የድርድሩን ሂደት በሚመለከት የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ  መግለጫ ሰጥተዋል።

ፓርቲዎቹ  ለመደራደር ከተስማሙባቸው አስራ ሁለት አጀንዳዎች ውስጥ በሁለቱ ላይ ድርድራቸው በመካሄድ መጠናቀቃቸውን አቶ ሽፈራው ተናግረዋል።

ድርድሩ የአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ እየተካሄደ እንደሚገኝም አቶ ሽፈራው ገልጸዋል።