አንጌላ መርኬል ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አስታወቁ

ህዳር 12፣2010

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬል በአገሪቱ ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

መራሂተ መንግስቷ ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ የፈለጉት በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ጥምር መንግስት ለመመስረት የተደረገው ድርድር ባለመሳካቱ ነው።

መራሂተ መንግስቷ በአስራ ሁለት ዓመት የቻንስለርነት ቆይታቸው አሁን ከባድ ፈተና ላይ ናቸው ተብሏል።

ሜርኬል ዜድ ኤፍ ከተሰኘ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጀርመን የሚያስፈልጋት እንጂ ለእያንዳንዱ ጉደይ የብዙሀን ድምጽ ውሳኔ አይደለም ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።