የካናዳ ኩባንያ በኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ዘርፍ ልማት መሰማራት እንደሚፈልግ አስታወቀ

ህዳር 12፣2010

ኢ ሲ ሲ የተባለ የካናዳ ኩባንያ በኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ዘርፍ ልማት መሰማራት እንደሚፈልግ አስታወቀ።

የኩባንያው ዋና ዳይሬክተር ጆርዳን አክስሊ በእንፋሎት ሃይል ልማት እና በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ መኪኖችን በኢትዮጵያ ለመገጣጠም በሚችልበት መንገድ ዙሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል ጋር ተወያተዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ፋብሪካውን ለማቋቋም የሚያስችለውን ጥናት እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል᎓᎓

አገሪቱ ለታዳሽ ሀይል ልማት የሰጠችው ትኩረት የኩባንያውን ትኩረት እንደሳበም የኩባንያው ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል᎓᎓

እንደዚህ አይነት ኢንቨስትመንቶች ለአገሪቱ እድገት ካላቸው ሚና አኳያ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል᎓᎓

ሪፖርተር:-መቅደስ ጥላሁን