የአፍሪካ ነፃ የንግድ ልውውጥ እና የኢንዱስትሪ ልማት ሊደጋገፉ እንደሚገባ ተገለጸ

ህዳር 12፣2010

የአፍሪካ የነፃ ንግድ ልውውጥ እና ኢንዱስትሪ መደጋገፍ እንደሚገባቸው የመንግስታቱ ድርጅትዋና ጸሀፊ  አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ።

ዋና ጸሐፊው የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካን ኢንዱስትሪ እድገት ቀን ሲከበር እንደተናገሩት የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና አህጉራዊ ነጻ የንግድ ልውውጥ መደጋገፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል᎓᎓

የዚህ አመት የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ቀን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት   በአፍሪካ  የቀጥታ ነጻ የንግድ ማእከል  ለማምጣት ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ አጉልቶ ያሳየናል  ብለዋል ሚስተር ጎቴሬስ᎓᎓

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ልማት፣ የአህጉራዊ የነፃ ንግድ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ለተቀናጀ ሰላማዊና የበለጸገ ማህበረሰብ የመገንባት ድጋፉን እንደሚቀጥል ዋና ጸሃፊው አረጋግጠዋል᎓᎓

ዋና ጸሀፊው የአፍሪካ ኢንዱስትሪ ልማት ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑን  ገልጸው  እ.ኤ.አ በ2030 የአፍሪካ አገራት ዘላቂ ልማት አጀንዳን ለማሳካት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ  እውን ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ማለታቸውን ከድርጅቱ ድረገጽ የተግኘውመረጃ ያመለክታል።