አሜሪካ የዱር አራዊት አደን እገዳ ዳግም አጸናች

ህዳር 11፣2010

አሜሪካ ሽራው የነበረውን ህጋዊ የዱር አራዊት አደን እገዳ ዳግም አጸናች፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናላድ ትራምፕ ውሳኔ በአፍሪካ በተለይም በዙምባቤና በዛምቢያ የሚገኙና ቁጥራቸው እየተመናመኑ የመጡትን የዝሆንና የአምበሳ ዝርያዎችን ለመታደግ የታሰበውን ውጥን የሚያሳካ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 በቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እየተተገበረ የቆየው ይህ ሽልማት የሚያስገኝ ህጋዊ የዱር አራዊት አደን እገዳ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስር በሚገኘው የሀገሪቱ የአሳና የዱር አራዊት አገልግሎት ተቋም ነበር የተሻረው ፡፡

በዚህም የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች፣ የእንስሳት መብት ተሟጋቾችና ጥቂት የሪፐፕሊካን ፓርቲ አባላት የፕሬዝዳንት ዶናላድ ትራምፕ ውሳኔን አውግዘው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ዳግም እንዲተገበር የወሰነው ህግ ሰዎች እራሳቸውን ለማዝናናት በህጋዊ የዱር አራዊት አደን ስም የዱር አራዊትን በመግደል የዝሆን ጥርስ የመሰሉ የእንስሳቶቹን አካል ወደ አሜሪካ እንዳያስገቡ የሚከለክል ነው፡፡

በሀገሪቱ ህዝብ ተቃውሞ ተሸሮ የቆየውን የዱር አራዊት አደን እገዳ ህግ ዳግም ቢፀድቅም በጉዳዮ ላይ ተጨማሪ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋዎች፡፡

ህጉ ተግባራዊ እንዲሆን የአሜሪካ አስተዳደር ቢፈቅድም የሀገሪቱ የአሳና የዱር አራዊት አገልግሎት ተቋም የዝሆን ጥርስ የመሰሉ የዱር አራዊት አካላትን ወደ አሜሪካ ለማስገባት ለሚፈልጉ ሰዎች ፍቃድ የመስጠት አገልግሎቱን እንደማያቋርጥ ነው የተናገረው፡፡

በባለፉት 9 ዓመታት ብቻ 20 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የዝሆን ቁጥር መመናመኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን ድረ-ገጽ