ወጣቶችን በማደራጀትና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ተጠየቀ

ህዳር 11፣2010

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ወጣቶችን በማደራጀትና በስራ ዕድል ፈጠራ  ላይ ጠንክሮ  እንዲሰራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትምህርትና  ስልጠና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

ኮሚቴው የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና  ስልጠና ኤጄንሲና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና  ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2010 መነሻ ዕቅድን ገምግሟል።

ዘርፉ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለጥቃቅንና አነስተኛ  ኢንተርፕራይዞች በመስጠት አምራቹ ዘርፍ እመርታዊ  እድገት እንዲኖረው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የቴክኒክና ሙያ  ስልጠና ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታው አቶ  ተሾመ ለማ ገልጸዋል።

ዘርፉ ወጣቶችን አደራጅቶ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ክትትልና ድጋፉን አጠናክሮ  እንዲያስቀጥል   ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።