የአማራና ትግራይ ክልል ህዝቦች የጋራ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ ጉብኝት አደረጉ

ህዳር 10፣2010

የአማራና ትግራይ ክልል ህዝቦች የጋራ የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ጎንደር የመጡ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ ጉብኝት አድርገዋል።

ተሳታፊቹ የፋሲል ቤተ መንግስትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የአማራና ትግራይ ህዝቦች በደም የተቆራኙ ብቻ ሳይሆን በታሪክም  የተሳሰሩ በመሆናቸው  እንዲህ ዓይነቱ የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነት የበለጠ የሚያጠናክሩ ሁኔታዎችን ማበራከት ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ ተካሂዶ በነበረው በአማራና ትግራይ ህዝቦች  የጋራ መድረክ ላይም ለዘመናት የቆየውን የሁለቱን ህዝቦች  መልካም ወንድማማችነት የሚያሻክሩ  ሁኔታዎችን በጋራ በመከላከል  ሊነጣጠል የማይችለውን የሁለቱን ህዝቦች አብሮነት በተጠናከረ ሁኔታ ማስቀጠል ይገባል የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡

ሪፖርተር፡‑ ፋሲካ አያሌው