ተመድ በሜዲትራኒያን ባህር የጸጥታ ችግርን ለመፍታት ሀገራት በትብብር እንዲሰሩ ጠየቀ

ህዳር 09፤2010

በሜዲትራኒያን ባህር ላይ እያጋጠሙ ያሉትን የጸጥታና ደህንነት ችግሮችን ለማስወገድ አለም አቀፉ ህብረተሰብ በትብብር እንዲሰራ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው እንደገለጹት ከሆነ በአካባቢው የአደንዛዥ እጽ ፤ የጦር መሳሪያ፤ የነዳጅ ምርቶች፤ ህገ ወጥ ስደተኞች ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ የሚታይበት ነው፡፡

የሜዲትራኒያን ባህር የሚፈለግበትን ጥቅም እንዲያበረክት ከተፈለገ የአካባቢው ደህንነትና ሰላም መረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የሊቢያና የሳህል አካባቢ ሃገራት የጸጥታ ሁኔታ አለመሻሻል፤ ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር ለስደተኞች ፍልሰት መጨመርና ለህገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪው ሁኔታዎችን እንዳመቻቸም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ከ2,800 በላይ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ ህይወታቸውን እንዳጠ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ