ድንጋይ ከሰልን ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ አለም አቀፍ ጥምረት ተመሰረተ

ህዳር 08፣2010

ድንጋይ ከሰልን  ከኃይል ምንጭ አማራጭነት ውጭ ለማድረግ  ብሪታንያና ካናዳ የሚመሩት የ20 አገራት ጥምረት ተመሰረተ፡፡

ሁለቱ አገራት የሚያስተባብሩት የሀያ አገራቱ ጥምረት የአየር ብክለት ዋነኛ  ምንጭ የሆነው የድንጋይ ከሰል ጥቅም ላይ እንዳይውል ለማድረግ ያለመ ጥምረት ነው በጀርመን ቦን እተካሄደ ባለው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ይፋ የሆነው፡፡

እንደ ፈረንሳይ፣ፊንላንድና ሜክሲኮ ያሉ የድንጋይ ከሰል ተጠቃሚ አገራት እ.ኤ.አ ከ2030 በኃላ ድንጋይ ከሰልን ከኃይል አቅርቦት አማራጭነት ውጭ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

ይሁንእንጂ እንደ ቻይና ፣ አሜሪካና ጀርመን ያሉ ቀዳሚዎቹ የድንጋይ ከሰል ተጠቃዎች የጥምረቱ አካል አለመሆናቸው ከወዲሁ ስጋት ፈጥሯል፡፡

በቦን በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተገኙ የተለያዩ አገራት ሚንስትሮች ቢያንስ የድንጋይ ከሰል ተጠቃሚ 50 አገራት ፖላንድ ላይ በሚካሄደው ቀጣዩ የተመድ  የአለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ጥምረቱን ተቀላቅለው የስምምነቱ አካል ይሆናሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

የአለማችን 40 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመረተው ከድንጋይ ከሰል ከመሆኑ አንፃር በአለም አቀፍ ደረጃ ድንጋይ ከሰልን ከኃይል ምንጭ አማራጭ ውጭ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፈታኝ ያርገዋል የሚሉም አልጠፉም፡፡

የዘርፉ ተመራሪዎች በዚህ ሳምንት ይፋ ባደረጉት ግኝታቸው ድንጋይ ከሰል ሁነኛ የጋርበን ጋዝ መገኛ በመሆኑ ለበካይ ካዝ ልቀት ዋነኛው ምንጭ መሆኑ  መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

እንዲያውም በአስገራሚ ሁኔታ እየጨመረ ያለውን የአለማችን ሙቀት መጨመር ለመቆጣጠር ካስፈለገ ድንጋይ ከሰልን በኃይል አማራጭነት ከመጠቀም መታቀብን የሚጠይቀበት ወቅት አሁን መሆኑንም ተመራማሪዎቹ አስገንዝበዋል፡፡

በቦኑ የአየር ንብረት ለውጥ  ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ያለችው ኢትዮጵያ በበኩሏ እ.ኤ.ኤ በ2025 ከካረቦን ልቀት የፀዳ ምጣኔ ሀብት ለመግንባት እየተንቀሳቀሰች መሆኗን በአካባቢ፣ደንና አየር  ንብረት ለውጥ ሚንስትሯ  በኩል አቋሟን ይፋ እድርጋለች፡፡

ሚንስትሩ ገመዶ ዳሌ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ እንዳሉት ኢትዮጵያ እየገነባቻቸው ያሉት ታዳሽ የኃይል ምንጮች የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግቧን እውን ለማድረግ አስማማኝ መሰረቶች መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ