ተመድ በሶማሊያና በኤርትራ ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማእቀብ እንዲራዘም ወሰነ

ህዳር6 ፣2010

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሶማሊያና በኤርትራ ላይ ጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ ማእቀብ ባለበት እንዲቀጥል በድምፅ ብልጫ ወስኗል፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት በ11 ድጋፍና በ4 ድምፀ ታእቅቦ ነው በሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ላይ የማእቀቡን ውሳኔ ባለበት እንዲፀና ያስተላለፈው፡፡

ውሳኔው ከመተላለፉ ሳምንት በፊት ኤርትራ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካለው አልሸባብ ጋር ግንኙነት እንደሌላት በመግለፅ ማእቀቡ እንዲነሳላት የተመድ ባለሙያዎች ቡድን ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡

በአሜሪካ ግፊት እኤአ ከ2009 ጀምሮ በኤርትራ ላይ የተጣለው ማእቀብ ያልተገባና የማይረባ ነው ስትል ኤርትራ አጣጥላዋለች፡፡     

በአልሸባብ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባት የምትገኘው ሶማሊያም ከፊል ማእቀቡ እንዲፀናባት የተደረገ ሲሆን በዚህ ምክንያት አገሪቱ ከአሸባሪ ቡድኑ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ አዳጋች እንደሚያደርግባት የደህንነት ታዛቢዎች ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካ ኒውስ