የኬንያ ፍርድ ቤት የዳግም ምርጫውን አቤቱታ ማየት ጀመረ

ህዳር 5፤2010

የኬንያ ፍርድ ቤት በዳግም ምርጫው ውጤት ደስተኛ ያልሆኑ ዜጎች የተሰበሰበውን አቤቱታ መመለከተ መጀመሩን አሶሸትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡

ኡህሩ ኬንያታ ማሸነፋቸውን በአወጁበት የመጀመሪያው ምርጫ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዳግም ምርጫውም ኡህሩ ኬንያታ ዳግም ማሸነፋቸው ቢገለፅም ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲጋ እና ደጋፊዎቻቸው ምርጫውን እንደማይቀበሉ ሲገልፁ ተደምጠዋል፡፡

ከፊሉም በምርጫው ሳይተፉ ቀርተዋል፡፡

በመሆኑም የምርጫውን ውጤት የሚቃወሙ እነዚህ ዜጎች ፊርማ አሰባስበው አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ እየተመለከተው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ አሶሸትድ ፕሬስ