የኤሌክትሪክ መኪናዎች መበራከት የነዳጅ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል

ህዳር 5፤2010

በሚቀጥሉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪናዎች ቁጥር በተገመተው መልኩ የሚያድግ ከሆነ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያለው የነዳጅ ዘይት ፍላጎት ሊቀንስ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ዓለም በአሁኑ ሰዓት አትኩሮቱን ያደረገው ታዳሽ ሃይልና የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል የሃይል ምንጭ ላይ በመሆኑ የነዳጅ ፍላጉቱ ሊቀንስ ይችላል ተብሏል፡፡

በፔትሮኬሚካልና ሌሎች የትራንስፖርት ዘዴዎች ውስጥ ያለው እድገትም እንደተጠበቀ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ታዳሽ ሃይልን ለማምረት የሚያስፈልገው ወጪ እየቀነሰ በመምጣቱ የፈረንጆቹን 2018 የነዳጅ ዋጋ ትመናን መቀነሱን ዓለም ዓቀፉ የኢነርጂ ማህበር አስታውቋል፡፡

ማህበሩ ባወጣው መረጃ መሰረት በፈረንጆቹ 2025 ድረስ 50 ሚሊዮን በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ መኪናዎች ሊመረቱ ይችላሉ፡፡

በ2040 ደግሞ ይህ ቁጥር ወደ 300 ሚሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

በተለይም ደግሞ ከጸሃይ ሃይል የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል እጅጉን የሚጨምር ሲሆን በዓመት እስከ 70 ጊጋዋትስ ሊመረት ይችላል፡፡

ምንጭ ፡ ሮይተርስ