ኢትዮጵያና ኳታር በንግድና ኢንቨስትመንት አብሮ ለመስራት ተስማሙ

ህዳር 5፤2010

ኢትዮጵያና ኳታር ያላቸውን ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ለማስተሳሰር ተስማሙ፣፡፡

ሁለቱ ሃገራት በቀጠናው ሰላም ዙሪያም በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኳታሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህመድ ቢን አብድራህማን ጋር በዱሃ ባደረጉት ውይይት ኳታር በአዲስ አበባ ለመገንባት ያቀደችው የልብ ህክምና  ማዕከል በቅርቡ እንደሚጀመር የኳታሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልፀዋል፡፡

በኳታሩ ኢሜር ግብዣ በዶሃ ጉብኝት የተገኙት  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በዶሃ ብሄራዊ ቤተመንግስት ይፋዊ የአቀባበል ስነስርአት ተደርጎላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለኢትዮጵያ የልማት ድጋፍ ከሚያደርገው በኳታር ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት ያደርጋሉ፡፡፡