ከአራት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የካርበን ልቀት መጨመሩ በፓሪሱ ስምምነት ላይ ስጋት ፈጥሯል

ህዳር 4፣2010

እ.ኤ.አ. በ2017 በአለም አቀፍ ደረጃ በአራት  አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የጨመረው የካርበን  ልቀት  በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ላይ ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል ተባለ፡፡

የካርበን ጋዝ ልቀቱ መጨመር ዋነኛ ምክንያት ቻይና ከኢኮኖሚዋ እድገት ጋር በተያያዘ  ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል ተጠቃሚ በመሆኗ ነው ተብሏል፡፡         

የዘርፉ  ተመራማሪዎች የጋዝ ልቀቱ መጨመር አንድ ጊዜ ብቻ ለመከሰቱ እርግጠኛ  እንዳልሆኑ ገልፀዋል፡፡.

እንደ  ተመራማሪዎቹ ገለፃ የክፍለ ዘመኑን  አደገኛ የአለም ሙቀት ለመቀነስ እ.ኤ.አ. ከ2020  በፊት የተቃጠለ የጋዝ  ልቀት መቀነስ አለበት፡፡

የተቃጠለ ጋዝ ልቀቱ ከ2006 እስከ 2014 ድረስ 3 በመቶ ጭማሪ  እያሳያ ቢሆንም  ከ2014 እስከ 2016 ድረስ ግን ቀንሶ ታይቶ ነበር ፡፡

ግሎባል ካርቦን ፕሮጀክት ባደረገው ጥናት የተያዘው 2017 ደግሞ  በሰው ሰራሽ እንቅስቃሴዎች ምክንያት በአለም አቀፍ ደረጃ የአለም ሙቀት  በ2 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ተመራማሪዎቹ እርገጠኛ ባይሆኑም ልቀቱ እየጨመረ መምጣቱንም አመላክተዋል፡፡

በፓሪስ በተደረሰው የአገራት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መሰረት የአለም ሙቀትን ከ2 ድግሪ ሴንቲግሬድ በታች እንዲሆን በማድረግ እስከ 1.5 ድግሪ እንዲወርድ መስራት ነበር ዓላማው፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ