ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው

ህዳር 04 ፣ 2010

ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው፡፡

የምስራቅ አፍሪካዋ ሶማሌላንድ ህዝብ ቀጣዩን ፕሬዝዳንታንቸውን በዛሬው ዕለት እየመረጡ ነው፡፡

በምርጫ ሂደቱ የአይን አሻራ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ተብሏል፡፡ይህም የአይን ብሌን አሻራን ለምርጫ ጥቅም ላይ በማዋል ሶማሌላንድን ከአለም የመጀመሪያ ያደርጋታል፡፡

ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሶስት እጩዎች ያቀረቡ ሲሆን ፣ 7 መቶ ሺህ ያህል መራጮች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

60 የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን እንደሚታዘቡም ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ ከ1991 የቀድሞው የሶማሊያ ወታደራዊ መሪ ሲያድ ባሬ መውደቅ በኃላ የራስ አስተዳደሯን በራሷ ያወጀችው ሶማሌ ላንድ ነፃነቷን ብታውጅም እስካሁን ግን እውቅና አላገኘችም፡፡

ብዙዎች የአሁኗ ሶማሊያ ሰላምና ልማት ግንባታ አስተማማኝ ከሆነ ፣ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ጋር ጭምር በፌደራላዊ ስርዓትም ቢሆን አንድ የመሆን ተስፋ ይኖራቸዋል ብለው ይከራከራሉ፡፡ይሁን እንጂ ሌሎች ደግሞ ሶማሌ ላንድ በራሷ ነፃ አገር መሆኗን ማወጇን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር አንድ አገር የመሆን ተስፋዋ በቀላሉ የሚታሰብ አይደልም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ